የ Lynnwood Link Connections ፕሮጀክታችንን የመጀመሪያ ደረጃ ስለምንጀምር ደስታ ተሰምቶናል፣ እናም እርስዎ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ እናቀርባለን።
Metro ለ Sound Transit ወደ ሰሜን ወደ Shoreline እና Snohomish ካውንቲ መስፋፋት በዝግጅት ላይ ነው። በ2025፣ Sound Transit Link light rail Northgate ን ከ Lynwood ጋር የሚያገናኙ አምስት አዳዲስ ጣቢያዎችን ይከፍታል።
Lynnwood Link Connections አዲሱን የ light rail ጣቢያዎች የሚደግፍ የተሻሻለ የአውቶቡስ አገልግሎት ይሰጣል። በአቅራቢያ ያሉ ማህበረሰቦችን በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል፣ Bothell፣ Kenmore፣ Lake Forest Park፣ Mountlake Terrace፣ North Seattle፣ እና Shoreline ያሉ ነዋሪዎችን ሀሳቦቻቸውን እንዲያጋሩን እያገኘናቸው ነው።
አዲስ የመጓጓዣ እድሎችን ለማቀድ ዋናው አካል በታሪክ ያልተገለገሉ ህዝቦች ተንቀሳቃሽነት እና ተደራሽነት ማሻሻል ነው።
በሰሜን ምዕራብ King County በ Lynnwood Link Connections በኩል ያለውን መጓጓዣ የወደፊትን ሁኔታ ለመቅረጽ የሚያግዙ አንዳንድ ጥሩ እድሎች እዚህ አሉ፦
- የመጓጓዣ ፍላጎቶችዎን በተመለከተ የዳሰሳ ጥናት ይውሰዱ።
- Mobility Board ን ለመቀላቀል ያመልክቱ (የሚከፈልበት የአመራር እድል) እና Metro ን ስለ ማህበረሰብ ተሳትፎ እና የመጓጓዣ አውታርዎን ለማዘመን ምርጥ መንገዶችን በተመለከተ ያማክሩ።
- Metro ን በማህበረሰብዎ ውስጥ ይፈልጉ ወይም የፕሮጀክት ማንቂያዎችን ለመቀበል ይመዝገቡ።
Mobility Board ላይ ፍላጎት አለዎት? የሚከተሉትን ሰዎች እንፈልጋለን፦
- በሰሜን ምዕራብ King County ውስጥ፣ የሚኖሩ፣ የሚሰሩ እና/ወይም የሚጓዙ።
- የመጓጓዣ ሹፌር የሆነ ወይም የመጓጓዣ ሹፌር የመሆን አቅም ያለው።
- እንደ ግለሰብ (እንደ ድርጅት ሳይሆን) አመለካከትን የሚያመጣ።
- በዘር እኩልነት፣ በትራንስፖርት ጉዳዮች እና በዕድሎች ተደራሽነት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማገናኘት ፍላጎት አለው።
ስለ Lynnwood Link ቅጥያ ተጨማሪ መረጃ በ Sound Transit ድህረ ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል ።
የእኛ Mobility Board ከመጓጓዣ ጋር በተያያዙ ከውሳኔ ሰጪነት በታሪክ የተተዉ እና በእነዚህ ውሳኔዎች ያልተመጣጠነ ተፅእኖ ያላቸውን የሰው ቡድኖች በእኩልነት እንዲወክል እንፈልጋለን። የሚከተሉት ማንነቶች እና ልምድ ያላቸው ሰዎች እንዲያመለክቱ በአጽንዖት እናበረታታለን። ጥቁር፣ ተወላጅ እና ቀለም ያላቸው ሰዎች፤ ስደተኞች እና ጥገኞች፤ ከእንግሊዝኛ ሌላ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች፤ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወይም ምንም ገቢ የሌላቸው ነዋሪዎች፤ እና አካል ጉዳተኞች።
እናመሰግናለን! ከእርስዎ እንደምንሰማ ተስፋ እናደርጋለን።
ጥያቄዎች? ማመልከቻው ለእርስዎ በኢሜይል ቢላክልዎ ወይስ በፖስታ ቢላክልዎ ይመርጣሉ? የ Lynnwood Link Connections ቡድንን በ haveasay@kingcounty.gov ወይም 206-263-1939 ላይ ያግኙ።