የደቡብ ሊንክ ግንኙነቶች፦ በደቡብ ኪንግ ካውንቲ ውስጥ ስለታሰቡት የመንገድ የተሻሉ ለውጦችን ለማወቅ የመረጃ ክፍለ ጊዜዎቻችንን ላይ ይገኙ

Link ligh rail

ይህ የብሎግ ልጥፍ በእነዚ ቋንቋዎች ይገኛል፡ English (እንግሊዝኛ) 简体中文 (ቀላል ቻይንኛ) 繁體中文 (ባህላዊ ቻይንኛ) Español (ስፓንኛ)

የሊንክ ላይት ባቡርወደ ደቡብ እየተዘረጋ ሳለ የኪንግ ካውንቲ Metro የደቡብ ሊንክ ግንኙነቶች የእንቅስቃሴ ፕሮጀክት በደቡብ ኪንግ ካውንቲ ውስጥ ላሉ ማህበረሰቦች የህዝብ መንገድን ለማሻሻል እየሰራ ነው።

ጃንዋሪ 7 ላይ የመጀመሪያውን የመስመር ላይ የመረጃ ክፍለ ጊዜን አካሂደናል። YouTube ላይ የተቀረጸውን ክፍለ ጊዜ መመልከት ይችላሉ። እንዲሁም ክፍለ ጊዜው በአማርኛበካንቶኒዝበማንዳሪን እና በስፓኒሽ ይገኛል።

በደቡብ ሊንክ ግንኙነቶች ፕሮጀክት ላይ ስለታቀዱትለውጦች የበለጠ ለማወቅ እና ጥያቄዎችን ለመጠየቅ በቀጣይ የመስመር ላይ የመረጃ ክፍለ ጊዜያችን ላይ እንዲገኙ እንጋብዝዎታለን፦

ሰኞ፣ ፌብሯሪ 10፣ ከምሽቱ 6። እዚህ ይመዝገቡ

አስተርጓሚ ካስፈለገዎት እባክዎ ከላይ ባሉት ማገናኛዎች ላይ የመረጃ ክፍለ ጊዜው ላይ በሚመዘገቡበት ወቅት አስተርጓሚ እንደሚፈልጉ ይንገሩን።

የምናባዊዎቹ ወይም የቨርቹዋሎቹ የመረጃ ክፍለ ጊዜዎች በ2026 መጀመሪያ ላይ ገልግሎቱን ለመጀመር የታቀደውን የሳውንድ ትራንዚት ፌደራልዌ ሊንክ ኤክስቴንሽን ፌደራልዌይ ሊንክ ኤክስቴንሽን Metro አገልግሎት ላይ ስለሚደረጉ ለውጦች የበለጠ ለማወቅ የሚረዱ ክስተቶች ናቸው።እስከ ፌብሯሪ 28 ድረስ Metro በደቡብ ኪንግ ካውንቲ ውስጥ ከሚኖሩ አሽከርካሪዎች፣ ነዋሪዎች እና ሰራተኞች አስተያየት ለማግኘት እየሞከረ ነው።

ወደ ፌደራልዌ የሚወስደው 1 መስመር በሲታክ እና ፌደራልዌ መካከል ያለውን ክልላዊ ቀላል ባቡር ስርዓት ላይ ስምንት ማይል ያህል ይጨምራል። ይህ ፕሮጀክት ኬንት-ደሞይንስ ውስጥ ከሃይላይን ኮሌጅ፣ ስታር ሌክ እና በፌደራልዌ መሃል ከተማ አጠገብ ያሉ ሦስት አዲስ ጣቢያዎችን ያካትታል።

Metro የአውቶቡስ አገልግሎት በተመለከተ በርካታ ማሻሻያዎችን እያቀረበ ነው። በተጨማሪም በአበርን፣ ቢውሬን፣ ደሞይንስ፣ ፌዴራልዌ፣ ኬንት፣ ኖርመንዲ ፓርክ፣ ፓሲፊክ፣ ሲታክ፣ ተክዊላ እና በአካባቢው ማዘጋጃ ቤት የማይተዳደሩ አንዳንድ የኪንግ ካውንቲ ከተማዎች ውስጥ በሚኖሩ የማህበረሰብ አባላት የመጀመሪያው ዙር የተሳትፎ ስብሰባ ላይ በሰጡት አስተያየት መሰረት የእርስዎን አስተያየት እየሰበሰበ ነው።

በእነዚህ የታሰቡ ለውጦች ላይ ዕቅዶቹን ለማጣራት የእርስዎን አስተያየት እንጠቀማለን፣ እንዲሁም በ2025 በጋ ወቅት ላይ ለማህበረሰብ ግምገማ እንዲያገለግል መረጃውን ያካፍላል።

ጥያቄዎች? የደቡብ ሊንክ ግንኙነቶች ቡድንን በ HaveASay@kingcounty.gov ላይ ያግኙ።

ምላሾትን ያስቀምጡ