በዚህ የክረምት ወቅት ከኪንግ ካውንቲ Metro ጋር ለመጓዝ የሚያገለግሉ ጠቃሚ ምክሮች
ይህ የብሎግ ልጥፍ በእነዚ ቋንቋዎች ይገኛል፡
የክረምቱ ወቅት ስለደረሰ በደህና እንዲጓጓዙ የኪንግ ካውንቲ Metro መሳሪያዎች መረጃ በመስጠት ያግዝዎታል።
ከመሄድዎ በፊት ይህን ይወቁ
- በክረምት የአየር ወቅት ጊዜ ስለአውቶቡስ፣ ስለአክሰስ ፓራትራንዚት የሚባሉ ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ የሆኑ ቋሚ መንገድ ያላቸው የህዝብ ማመላለሻዎች፣ ስለ ጎዳና መኪናዎች፣ ስለኪንግ ካውንቲ የውሃ ታክሲ ወይም ስለተፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ የ Metro Flex መጓጓዣዎች ጠቃሚ ምክሮችን ለማግኘት የ MetroWinter.com ድህረ-ገጽን ይጎብኙ። በድህረ-ገጹ ላይ የእንግሊዝኛን ቋንቋ ጨምሮ ስምንት ቋንቋዎች ይገኛሉ። እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ ቋንቋዎች በGoogle ተርጓሚ መሳሪያ በኩል ይገኛሉ።
- የበረዶ መንገድ ምንድን ነው? አውቶቡሶች በመንገድ ሁኔታ ምክንያት የመደበኛ መስመሮቻቸውን መጠቀም ካልቻሉ፣ የበረዶ መስመር የሚባሉትን ሌሎች አማራጭ መንገዶችን ሊጠቀሙ ይችላሉ። ለእርስዎ የአውቶቡስ መስመሮች የበረዶ መንገዶችን አስቀድመው ይመልከቱ። ዝማኔዎች በMetro የአገልግሎት ምክሮች ድህረ-ገጽ ላይ ይለጠፋሉ።
- የክረምት በረዶ በራሪ ወረቀቶች በአውቶቡሶች እና በሌሎች መጓጓዣ አገልግሎቶች ላይ ይገኛሉ፣ እንዲሁም አጋዥ የጉዞ ምክሮችን እና መረጃዎችን ያካትታሉ።
- በአውቶቡስ መስመርዎ ላይ ስለሚደረጉ ለውጦች ዝማኔዎችን ይፈልጋሉ? ስለሚጠቀሙባቸው መንገዶች እና አገልግሎቶች ጽሁፍ ወይም ኢሜል ለማግኘት የመተላለፊያ ማንቂያዎች ላይ ይመዝገቡ። አስቀድመው ተመዝግበዋል? በመላው የኪንግ ካውንቲ ላይ አዲስ መስመሮችን ስንጨምር እንዲደርስዎት ምዝገባዎችዎን ይገምግሙና የሚያስፈልጉትን ነገሮች ያስተካክሉ።
- በአውቶቡስ መስመርዎ ላይ ተለዋጭ ሌላ መንገድ ወይም ጊዜያዊ ለውጦች? ከመጓዝዎ በፊት መስመርዎ በግንባታ ምክንያት የተዘጋ መሆኑን ወይም አደጋ በሚያደርሱ የመንገድ ሁኔታዎች ምክንያት መቀየሩን ለማየት የእኛን የአገልግሎት ምክሮች ድህረ-ገጽን ይመልከቱ።
- ለአጠቃላይ መረጃ፣ ማንቂያዎች እና ዋና የጉዞ መስተጓጎል መረጃ የእኛን የማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎች በX (@KingCountyMetro) እና Facebook (@kcmetro) ላይ ይከተሉ።
- ከከተማዎ፣ አከባቢዎ እና ግዛትዎ ማንቂያዎች ወይም የማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎች ጋር በመገናኘት በአካባቢዎ ስላለው የመንገድ ሁኔታ ወቅታዊ መረጃ ያግኙ።
- በአስከፊ የአየር ሁኔታ ጊዜ፣ አስፈላጊ ከሆነ ብቻ ይጓዙ።
- Metro በመጥፎ የአየር ጠባይ ወቅትም የመሳፈሪያ ክፍያዎችን ይቀበላል። ነገር ግን፣ ኦፕሬተሮቻችን በደህንነት ሁኔታዎች ምክንያት፣ ለምሳሌ በቀዝቃዛ ጊዜ ወደ ማሞቂያ ማእከል ወይም በበጋ ሙቀት ምክንያት ወደ ማቀዝቀዣ ማእከል ለመሄድ የመጓጓዣ አገልግሎቶችን ለሚጠቀሙ ሰዎች፣ የመሳፈሪያ ክፍያ አለመኖርን እንደማገጃ አይጠቀሙም።
የአሁናዊ ጊዜ ዝማኔዎች
ጉዞዎ እየሠራ እንደሆነ፣ የሚነሳበትን ጊዜ ወይም እንደተዘረዘ ለማወቅ የአሁናዊ ዝማኔዎችን ያግኙ።
- ወደ መንገድዎ የሚሄዱትን ቀጣይ የአውቶቡስ ጉዞዎች ዝርዝር ለመቀበል የአውቶቡስ ማቆሚያ ቁጥርዎን ለ 62550 በስልኮ ጽሁፍ ይላኩ። እያንዳንዱ ጉዞ የሚገመተውን የመድረሻ ጊዜ፣ “scheduled” (መርሐግብር የተያዘለትን) ወይም “canceled” (የተሰረዘውን) ያሳያል። ለማስታወስ እንዲረዳዎት 62550ን አስቀድመው በስልክዎ ይመዝግቡ። በተጨማሪም ቁጥሩ በአውቶቡስ ማቆሚያዎች ላይም ተለጥፎ ይገኛል።
- የቀጣዩ መነሻዎች መረጃ በMetro የጉዞ እቅድ አውጪ ገጽ በላይኛው ቀኝ ጥግ ላይ ይገኛል።
ሌሎች የMetro አገልግሎቶች
የክረምቱ አየር ሁኔታ፣ አውቶቡሶች ውጭ ሌሎችንም የመጓጓዣ አገልግሎቶች እንዲዘጉ ወይም እንዲዘረዙ ሊያድረግ ይችላል። እባክዎ ከመጓዝዎ በፊት በድጋሚ ያረጋግጡ። የውሃ ታክሲ፣ Metro Flex እና አክሰስ ፓራትራንዚት የሚባሉ ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ የሆኑ ቋሚ መንገድ ያላቸው የህዝብ ማመላለሻዎች መረጃ በድህረ-ገጾቻቸው ላይ ይለጥፋሉ። የአክሰስ (Access) ተጠቃሚዎች ተጠቃሚዎች ለአክሰስ የትራንስፖርት ጥሪ ማዕከል በ (206) 205-5000 መደወል ይችላሉ።
በአስተማማኝ እና በምቾት ይሳፈሩ
- መንገዶች በረዷማ ሲሆኑ ወይም የሚያዳልጥ በረዶ ሲይዙ፣ እባክዎን አውቶቡስዎን ለጥ ባለ መንገዶች ላይና ከዳገቱ ጫፍ ላይ ወይም ከታች ባሉት የአውቶቡስ ማቆሚያዎች ላይ ይጠብቁ፣ ወይም የመንገድ ሁኔታዎች በበረዶ ማስወገጃ በሚጸዱበት ቦታ ላይ ያቁሙ።
- አስታውሱ፣ ፀሐይ ቀደም ብላ ስለምትጠልቅ፣ ለማየት ያስቸግራል። የእጅ ባትሪ ወይም ስልክ መጠቀም ለሹፌሩ በአውቶቡስ ማቆሚያው ላይ እንዳሉ ለማሳወቅ ጥሩ መንገድ ነው።
- ሁኔታዎች አገልግሎቱን ሊያዘገዩ ይችላሉ፣ ስለዚህ ዝግጁ ይሁኑ! ጉዞዎን ሲጠብቁ ለአየር ሁኔታ ተስማሚ የሆኑ ልብሶችን እና ጫማዎችን ይልበሱ።
