የሬንተን አካባቢ ተንቀሳቃሽነት ፕሮጀክት ቦርድን ይቀላቀሉ እና የህዝብ መጓጓዣ የወደፊት ሁኔታ ለመቅረጽ ያግዙ
ይህ የብሎግ ልጥፍ በእነዚ ቋንቋዎች ይገኛል፡
ለውጦች ወደ ሬንተን እየመጡ ነው – እና የKing County Metro እርስዎ እንዲሳተፉ ይፈልጋል! በከተማው ውስጥ የሚኖሩ፣ የሚሰሩ ወይም የሚጓዙ ከሆነ፣ ይህ ወሳኝ የህዝብ መጓጓዣ አገልግሎት ልማት ለመቅረጽ እድልዎ ነው። Metro የሬንተን አካባቢ ተንቀሳቃሽነት ፕሮጀክት ቦርድ አባላትን እየፈለገ ሲሆን ይህም በዳውንታውን ሬንተን እና በቅርቡ በSouth Renton Park and Ride (ሳውዝ ሬንተን ፓርክ ኤንድ ራይድ) አቅራቢያ የሚገነባው የRenton Transit Center (የሬንተን ህዝብ ማጓጓዣ ማዕከል) ዋና የዲዛይን ለውጥ የሚያንጽ በማህበረሰብ የሚመራ ቡድን ነው።
ይህ አዲስ ማዕከል – በMetro እና በSound Transit በጋራ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት – ሲሆን 2028 ላይ ስራ ሲጀምር ሬንተንን ከቡሪን እና ከቤሌቭዌ ጋር በSound Transit ፈጣን እና ተደጋጋሚ Stride BRT S1 Line በኩል ያገናኛል። ድምፅዎ ጉዞውን ለመምራት ይረዳል።
Metro የማህበረሰብ ግብረመልስ እና ምክሮችን በሚከተሉት ላይ ይፈልጋል፦
- የMetro መደበኛ መስመር እና ተለዋዋጭ አገልግሎቶች የአውቶቡስ አገልግሎት ዕቅዶች እና ማሻሻያዎች።
- በእቅድ አወጣጥ ሂደት ውስጥ የአሁን እና ሊሆኑ የሚችሉ ደንበኞች ሁሉን አቀፍ የማህበረሰብ ተሳትፎን ማረጋገጥ።
ማመልከት ያለበት ማን ነው?
በሬንተን ከተማ የሚኖሩ፣ የሚሰሩ ወይም የሚጓዙ ሰዎች። ከአሁን እና የወደፊት የህዝብ መጓጓዣ ተሳፋሪዎች፣ ማህበረሰብ ላይ ከተመሰረቱ ድርጅቶች አባላት፣ ከአካባቢ ንግዶች እና ደንበኞቻቸው ወይም ሰራተኞቻቸው በሬንተን ከተማ ከሚኖሩ፣ ከሚሰሩ ወይም ከሚጓዙባቸው ተቋማት የተወጣጡ የተለያዩ አባላት ያለው ቦርድ ለማቋቋም ፍላጎት አለን። በህዝብ ማጓጓዣ-ውሳኔ አሰጣጥ ተጽዕኖ ያረፈባቸው ወይም በታሪክ የተገለሉ ሰዎች እንዲያመለክቱ እናበረታታለን። ይህም ጥቁር፣ የአገሬው ተወላጆች እና ቀለም ያላቸው ሰዎች፤ የአካል ወይም የአእምሮ (ኮግኒቲቭ) እክል ያለባችው ሰዎች፤ ዝቅተኛ ወይም ምንም ገቢ የሌላቸው ሰዎች፤ ስደተኞች እና ጥገኞች፤ እና በቋንቋ የተለያዩ ማህበረሰቦችን ያካትታል። እንዲሁም ከአረጋውያን፣ ተማሪዎች እና ወጣቶች፣ እና በእነዚያ ቡድኖች ውስጥ እንደ LGBTQIA+ ብለው ራሳቸውን ከሚለዩ ሰዎች ውክልና እንፈልጋለን።
ምን መጠበቅ እንዳለብዎት
የሬንተን አካባቢ የተንቀሳቃሽነት ፕሮጀክት Mobility Board ከ2026 መኸር እስከ 2027 መኸር ባለው አንድ ዓመት አካባቢ ንቁ ሆኖ ይቆያል፣ ይህም በዓመት ውስጥ በግምት ከሶስት አራት ሰዓታት ወይም 10-16 ሰዓታትን ስብሰባዎችን ያካሄዳል። ስብሰባዎች የመስመር ላይ አማራጭ እያለ በቨርቹዋል መስመር ላይ ወይም በአካል ይከናወናሉ። (እንደ ተሳታፊው ተገኝነት መሰረት ቀጠሮ ይዘጋጅለታል።) የማህበረሰብ አባላት በሰአት $75 ይከፈላቸዋል። አባላት በቀላል ቋንቋ በህዝብ መጓጓዣ እቅድ አወጣጥ ላይ ስልጠና ያገኛሉ። ተጨማሪ ድጋፎች ሊቀርቡ ይችላሉ።
የእኛን የመስመር ላይ የማመልከቻ ቅጽ በመጠቀም ያመልክቱ።. የሬንተን አካባቢ ተንቀሳቃሽነት ፕሮጀክት ቦርድ ማመልከቻዎች እስከ ኦገስት 15፣ 11:59 p.m. ድረስ ተቀባይነት አላቸው።
ከማመልከቻ በኋላ
ትክክለኛ የመገኛ መረጃ የሚያቀርቡ አመልካቾች ማመልከቻ እንደገባ ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል። አጫጭር ቃለመጠይቆች የኦገስት 31 ሳምንት ላይ ሊደረጉ ይችላሉ፤ እና የመጨረሻው ምርጫ ደግሞ በሴፕቴምበር መጀመሪያ ላይ ይካሄዳል። የመጀመሪያዎቹ ስብሰባዎች በሴፕቴምበር 2026 አጋማሽ ላይ የሚካሄዱ ሲሆን በቦርዱ አባላት መገኘት ላይ በመመስረት ትክክለኛውን ቀን እና ሰዓት ይወስናል።
