RapidRide በ2032 ወደ ደቡብ Seattle እየመጣ ነው!
ይህ የብሎግ ልጥፍ በእነዚ ቋንቋዎች ይገኛል፡
በደቡብ Seattle ውስጥ የሚሰራ የመጀመሪያው RapidRide Line ይሆናል ፣ ይህም በKing County ውስጥ ካሉት በጣም ስራ ከሚበዛባቸው የአውቶቡስ ኮሪደሮች በአንዱ ላይ ተደጋጋሚ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን እንዲህም የህዝብ መጓጓዣውን Rainier Valley ውስጥ ካለው Link light rail 1 መስመር ጋር ያገናኛል። RapidRide R Line ከDowntown Seattle፣ Chinatown-International District (Little Saigon ጨምሮ)፣ Mount Baker፣ Columbia City፣ Hillman City፣ Brighton፣ Dunlap፣ Rainier Valley እና Rainier Beach ያሉትን የመኖሩያ መንደሮች የሚያገለለውን የአሁኑን Route 7 ያሻሽላል።
የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ምልከታ
Route 7 በMetro ውስጥ ካሉት በጣም ሥራ ከሚበዛባቸው መንገዶች አንዱ ሲሆን በየቀኑ ከ11,000 በላይ ሰዎችን ያገለግላል። በ2032 አገልግሎት እንዲመጀመር የታቀደው የRapidRide R Line በሚከተሉት የመንገዱ ማሻሻያዎች አማካኝነት የህዝብ መጓጓዣ የጉዞ ጊዜን፣ አስተማማኝነትን እና የተሳፋሪዎችን ተሞክሮ ለማሻሻል ያለመ ነው፦
- የተሻሻሉ የመጓጓዣ ጣቢያዎች እና መጠለያዎች
- የተሻሻለ የመብራት እና የተሳፋሪ መገልገያዎች
- የአውቶቡስ ብቻ መስመሮች
- መዘግየቶችን ለመቀነስ የምልክት ማሻሻያዎች
- ለእግረኞች ደህንነቱ የተጠበቀ የመጓጓዣ መዳረሻ
ለRapidRide R Line እቅድ ማውጣት ይቀጥላል
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በተፈጠሩ የገንዘብ ድጋፍ ችግሮች ምክንያት የዲዛይን ስራው ከተቋረጠ በኋላ Metro RapidRide R Line በማስጀመር ወደፊት እየገሰገሰ ነው። ፕሮጀክቱ በተቋረጠበት ወቅት፣ ኮሪደሩ ማደጉንና መለወጡን ቀጥሎ ነበር። የSeattle Department of Transportation (SDOT፣ የሲያትል የትራንስፖርት መምሪያ) እና የWashington State Department of Transportation (WSDOT፣ የዋሽንግተን ስቴት የትራንስፖርት መምሪያ) የመኪና መንገድ፣ የእግረኛ መንገድ እና የመስቀለኛ መንገዶች ማሻሻያዎችን አጠናቀዋል፣ እና በመንገዱ ዳር አዳዲስ ቤቶችና የንግድ ሱቆች ተገንብተዋል።
ፕሮጀክቱ ወደፊት እንዲራመድ ለማዘጋጀት፣ Metro እነዚህን ለውጦች ገምግሞ የRapidRide R Line ዲዛይን አሁን ያለውን ሁኔታ ለማንፀባረቅ እያዘመነ ነው። ይህ ሥራ በቅርብ ጊዜ በተደረጉ ኢንቨስትመንቶች ላይ ለመገንባት ይረዳል፣ የተጠናቀቁ ማሻሻያዎችን ድግግሞሽ ይከላከላል፣ እና ፕሮጀክቱ ለቀጣዩ የዲዛይን ደረጃ ዝግጁ መሆኑን ያረጋግጣል።
በክፍት ስብሰባ ላይ ይቀላቀሉን
ስለ RapidRide R Line ፕሮጀክት ይወቁ፣ ጥያቄዎችን ይጠይቁ እና በሚመጣው ክፍት ስብሰባ ላይ አስተያየትዎን ያጋሩ።
በአካል
- ረቡዕ፣ ኦገስት 12 በRainer Beach Library ከ5pm እስከ 7pm
- ሐሙስ፣ ኦገስት 13 በBeacon Hill Library ከ5:30 pm እስከ 7:30 pm
በቨርቹዋል
- ረቡዕ፣ ኦገስት 19 ከቀትር እስከ 1pm
- ቅዳሜ፣ ኦገስት 22 ከ11am እስከ ቀትር
የማህበረሰብ ተሳትፎ
ፕሮጀክቱ ከመቆሙ በፊት፣ ከጁን 2019 እስከ ማርች 2020 ባለው ጊዜ ውስጥ፣ Metro በታቀደው RapidRide R Line ላይ ያሉ ማህበረሰቦች አነጋግሯል።
የመጀመሪያው ምዕራፍ የRainier Valley ነዋሪዎችን በማሳተፍ፣ ፕሮጀክቱን በማስተዋወቅ እና በትራንስፖርት ፍላጎቶች ላይ ግብዓት በማሰባሰብ ላይ ያተኮረ ነበር።
ሁለተኛው ምዕራፍ የታቀዱ የጣቢያ ቦታዎችን ማጋራት፣ ግብረመልስ መሰብሰብ እና ሆን ተብሎ የተዘጋጀ፣ ሁሉን አቀፍ የተደራሽነት አገልግሎት መስጠትን ያካትታል፤ ይህም አጭር መግለጫዎችን፣ የእግር ጉዞ ጉብኝቶችን፣ በአካል እና በመስመር ላይ ክፍት ስብሰባዎች በተለያዩ ቋንቋዎች ማቅረብን፣ በማህበረሰብ ዝግጅቶች እና በአውቶቡስ ማቆሚያዎች ላይ መግባባትን እና ከማህበረሰብ ቡድኖች፣ Route 7 ኦፕሬተሮች እና ከተመረጡ ባለስልጣናት ጋር መነጋገርን ያካትታል። የጣቢያ ቦታዎች፣ የመዳረሻ ማሻሻያዎች እና የመንገድ ማሻሻያዎች ላይ የማህበረሰብ አስተያየት በቀጥታ የተመረጠውን ፅንሰ ሀሳብ ለመቅረጽና ለማሻሻል ረድቷል።
በሦስተኛው የተሳትፎ ምዕራፍ፣ Metro ስለ መጨረሻው preferred concept መረጃ አጋርቷል። ይህም የጣቢያው ቦታዎች፣ የታቀዱ ባህሪያት፣ የአውቶቡስ ፍጥነትን እና አስተማማኝነትን የሚያሻሽሉ ፕሮጀክቶች እና ወደ አውቶቡሱ ለመድረስ ቀላል እና ደህንነቱ የተጠበቀ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን ያካትታል።
Metro ይህንን ሥራ እንደገና ስለጀመረ፣ ፕሮጀክቱ የታቀደውን ሥራ እንደገና በማስተዋወቅ እና የማህበረሰብ አባላትን እንደገና በማሳተፍ የመጨረሻውን የተሳትፎ ምዕራፍ ይቀጥላል። የተሳትፎ እንቅስቃሴዎች በመኖሪያ አካባቢዎች ሁሉ ተደራሽነትን፣ የቤት ባለቤቶችን ማሳተፍን፣ ምናቨርቹዋል እና በአካል የሚሳተፉባቸው ክፍት ስብሰባዎችን ማስተናገድን፣ ድህረ ገጹን ማዘመንን እና ጥያቄዎች ሲነሱ አጭር መግለጫዎችን ማቅረብን ያካትታሉ። የተሳትፎው ምዕራፍ ከኦገስት 1 እስከ 31፣ 2026 ድረስ ይቆያል።
[DG1]I included our August dates
[LE2]Waiting to hear from Mark when website will launch.
በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያዌዎች
- RapidRide R Line ምን ያህል ርዝመት አለው?
የወደፊቱ R Line በDowntown Seattle እና በRainier Beach በኩል በግምት ስምንት ማይል ያህል ይዘልቃል። የህዝብ መጓጓዣ ኮሪደሩ በርካታ መንደሮችን አቋርጦ ወደ መኖሪያ ቤት፣ ሥራ፣ ትምህርት ቤቶች፣ የሕዝብ አገልግሎቶች እና መጓጓዣ የሚያገናኙ እና የሚመጡ ግንኙነቶችን ያቀርባል። Rainier Avenue S የጭነት መኪናዎች የአካባቢውን ንግዶች ማገልገል እንዲችሉ ሰፊ መስመር የሚፈልግ የተወሰነ የጭነት መስመር መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ በSeattle ውስጥ ካለ ከማንኛውም ኮሪደር ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛውን የግጭት አደጋዎች ቁጥር አለው። የታቀዱት የR Line ለውጦች አስተማማኝነትን እና የመጓጓዣ ጊዜን ከማሻሻል ባለፈ ለሁሉም የአካባቢው ተጠቃሚዎች ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ይፈጥራሉ። - King County Metro የቤት ባለቤቶችን ያነጋግራል?
ቤቶች ላይ የሚኖሩ ተጽዕኖዎች ከተለዩ፣ የቤቱ ባለቤት ይገናኛል። የቤት ባለቤቶች ካልተገናኙ፣ በቤቱ ላይ የታቀደ ተጽእኖ የለም ማለት ነው። የተፅዕኖው ደረጃ ምንም ይሁን ምን፣ በመንገዱ ላይ ያሉ ሁሉም የቤት ባለቤቶች በፕሮጀክቱ ሂደቶች በሙሉ የፕሮጀክት ማሳወቂያዎችን መቀበላቸውን ይቀጥላሉ። - በPrentice Loop ላይ ምን ይከሰታል?
RapidRide R Line በRainier Beach Link ጣቢያ እንዲጠናቀቅ ታቅዷል፣ እና Metro የR Line አገልግሎት ሲጀምር ከS Henderson Street በስተደቡብ ወደሚገኙ አካባቢዎች የሚመጡ እና የሚጓዙ ሰዎችን እንዴት እንደሚያገናኝ እየገመገመ ነው። እንደዚህ ሥራ አካል፣ Metro ከS Henderson Street በስተደቡብ ያሉ ማህበረሰቦችን የመጓጓዣ ፍላጎቶቻቸውን በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት እና የወደፊት የመጓጓዣ አገልግሎት ውሳኔዎችን ለማሳወቅ ከእነሱ ጋር ይወያያል። ግቡ የህዝብ መጓጓዣ አገልግሎቱ ተደራሽ፣ አስተማማኝ እና ለመረዳት ቀላል ሆኖ እንዲቆይ ማድረግ ነው። - ስለ Metro የእንክብካቤ እና ተገኝነት አቀራረብ የበለጠ የት መማር እችላለሁ?
የMetro የእንክብካቤ እና ተቀገኝነት አቀራረብ ንፁህ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የበለጠ ተቀባይነት ያለው የህዝብ መጓጓዣ ስርዓት በመፍጠር ላይ ያተኩራል። Metro ንፅህናን እንዴት እንደሚያሻሽል፣ የሰራተኞችን ተገኝነት እንዴት እንደሚያሳድግ፣ ተሳፋሪዎችን እንደሚደግፍ፣ ግልጽ የሆኑ ተጠባቂ ግቦችን እንዴት እንደሚያስቀምጥ እና አውቶቡሱን ለመሳፈር፣ የዊልቸር ወይም የመንቀሳቀሻ እርዳታን ለመጠቀም እና በብስክሌት ስለመጓዝ የደህንነት ምክሮችን እንዴት እንደሚሰጥ ይወቁ። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የMetro የተሳፋሪ ድህንነት ድህረ ገጽ ይጎብኙ።


