Metro የRoute 106 መሥመርን ለማሻሻል ጥናት እያደረገ ነነው
ይህ የብሎግ ልጥፍ በእነዚ ቋንቋዎች ይገኛል፡
King County Metro ከ Seattle Department of Transportation (SDOT)፣ King County Road Services እና City of Renton ጋር በመተባበር የRoute 106ን የአገልግሎት መሥመር ለማሻሻል ማለትም የአውቶቡስ ጉዞ የሚወስደውን ሰዓት ለማሳጠር፣ የአገልግሎቱን አስተማማኝነት ለመጨመር፣ እንዲሁም ለተገልጋዮች የሚያረካ አገልግሎት ለመስጠት ጥናት እያደረገ ነው። Route 106 በየቀኑ ከ5000 በላይ ተገልጋዮችን ያስተናግዳል። በአብዛኛው ቀኖች ከ10 እስከ 15 ደቂቃዎች ውስጥ እየተከታተለ ይመጣል። ይህ መሥመር International Districtን፣ Mt. Baker ን፣ Rainier Valley ን፣ Skyway ን እና downtown Renton ን ያገናኛል። በእነዚህ ሰፈሮች ውስጥ የሚኖሩ ብዙ ነዋሪዎችም ወደ ሥራ፣ ትምህርት ቤት እንዲሁም ወደ ልዩ ልዩ አስፈላጊ አገልግሎቶች ለመድረስ መሥመሩን ይጠቀማሉ።

Route 106 የሚያገለግላቸው ማኅበረሰቦች በእኛ የ Mobility Framework ውስጥ “ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች ያሉባቸው ስፍራዎች” ተብለው የሚጠሩ ናቸው። ይህ ምድብ ከፍተኛ የሆነ ዝቅተኛና ከዝቅተኛ በታች የሆነ ገቢ ያላቸው፣ ባለቀለም ቆዳ ያላቸው ማኅበረሰቦች፣ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች፣ ብዝኃ ቋንቋ ያላቸው ማኅበረሰቦች እና ሌሎች በሚገባ ማኅበረሰባዊ አገልግሎት ያላገኙ ሰዎችን ሁሉ ያካትታል።
የ Route 106 ጥናት ለሚከተሉት ጉዳዮች ምን መደረግ እንደሚገባው ለማወቅ ነው።
- የአውቶቡስ ጉዞ የሚወስደውን ሰዓት ከ10 እስከ 15 ፐርሰንት ለመቀነስ
- አውቶቡሶች ለእነርሱ በተዘጋጀላቸው ኮሪደር የበለጠ አስተማማኝ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ
- ከRoute 106 ወደ ሌሎች የመጓጓዣ መንገዶች የሚደረግ ዝውውርንም ለማሣለጥ
- አሁን ያሉትን ተገልጋዮች በመጥቀም የተገልጋዮችን ቁጥር ለመጨመር
ሊሻሻሉ የሚችሉ ነገሮች፤ ምንድናቸው? መሻሻል ያለባቸውስ ለምንድነው?
የ Route 106 ጥናት የጉዞ መሥመሩ ፈጣንና አስተማማኝ ጉዞን በሺዎች ለሚቆጠሩ ተገልጋዮቹ በየቀኑ ለማቅረብ መሻሻል ያለባቸውን ነገሮች ለይቶ ለማወቅ የሚደረግ ነው። ከዚህ በታች የመሥመሩን አገልግሎት ለማሻሻልና ቁጥሩ በፍጥነት እየጨመረ የመጣውን ማኅበረሰብ ፍላጎት ለማርካት እየታሰቡ ያሉ የማሻሻያ ምሳሌዎች ቀርበዋል።
| የማሻሻያ ዓይነት | ምንድነው | ጠቃሚነቱ ምንድነው |
|---|---|---|
| አውቶቡሶችን የሚያሳልፍ የትራፊክ መብራት | አውቶቡሶች ውስጥ የሚገጠምና የትራፊክ መብራቶች ጋር ሲደርስ መብራቱ አውቶቡሶቹን እንዲያልፉ አረንጓዴ እንዲሆን የሚያደርግ ሽቦ አልባ የግንኙነት ሥርዓት ነው። | ይህ ሥርዓት አውቶቡሶች በመብራት ላይ በመቆም እንዳያጠፉ ያደርጋል። በዚህም የጉዞ ሰዓትን ይቀንሳል። |
| የአውቶቡስ ፌርማታዎችን ማሸጋሸግ ወይም ማስወገድ | በጣም ቅርብ ለቅርብ የሆኑ ፌርማታዎችን ያሸጋሽጋል። | በጉዞ መሥመሩ ላይ ቅርብ ለቅርብ የሆኑ ፌርማታዎችን በማሸጋሸግ አውቶቡሶች ብዙ በመቆም ጊዜ እንዳያጠፉ ያደርጋል። ይህም የጉዞ ሰዓትን ይቀንሳል። |
| መንገድ ውስጥ የሚሠሩ የአውቶቡስ መቆሚያዎች | አውቶቡሶች መንገደኞችን ለመጫንና ለማውረድ ወደ መንገድ ዳር መውጣት ሳያስፈልጋቸው በመንገድ ውስጥ እያሉ ለመቆም፣ ለመጫንና ለማውረድ እንዲችሉ የሚያደርግ ሥርዓት ነው። | ይህ ሥርዓት አውቶቡሶች ለመጫንና ለማውረድ ሲሉ ወደ መንገድ ዳር ለመውጣት እንዳይገደዱ ያደርጋል። ይህም ተገልጋዮች እንዳይቸገሩ ያደርጋል። እግረኞችና ብስክሌተኞችም በቀላሉ መንገዱን እንዲጠቀሙ ያስችላቸዋል። |
| ሰልፉን መቅደም መቻል | አውቶቡሶች ለአውቶቡስ ከተሠመረው መሥመር ወይም ከቀኝ መታጠፊያ መሥመር ወደ መደበኛው መሥመር እንዲገቡ የሚፈቅድ ሥርዓት ነው። | አውቶቡሶች በአካባቢያቸው ከሚገኙት መኪኖች ቀድመው እንደልባቸው እንዲንቀሳቀሱ በመፍቀድ የጉዞ ሰዓትን ያሳጥራል። |
| የ Business Access and Transit (BAT) መሥመሮች ወይም የአውቶቡስ መሥመሮች | ለአውቶቡሶች ብቻ ወይም (በዋናነት ለአውቶቡሶች) የተፈቀዱ መሥመሮች ናቸው። | ይህ ሥርዓት አውቶቡሶች ለእነርሱ ብቻ በተዘጋጀላቸው መሥመር ላይ በመጓዝ በፍጥነት እንዲጓዙ ያደርጋል። በዚህም የጉዞ ሰዓትን ይቀንሳል። |
ከሴፕቴምበር 8 እስከ ኦክቶበር ሦስት ድረስ Metro ተገልጋዮችን፣ የንግዱን ማኅበረሰብ፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ የማኅበረሰብ አባላትን በማነጋገር Route 106ን ለማሻሻል በሚሆኑት ሐሳቦች ላይ ምላሾችን ያሰባስባል። ይህም የቀረቡትን የማሻሻያ ሐሳቦች ለማስጨበጥ ይረዳል።
Metro ለማወቅ የሚፈልጋቸው ነገሮች፣
- Route 106ን እንዴት እየተጠቀሙ እንደሆነ
- Route 106ን አስመልክቶ ያለዎትን አስተያየት
- በRoute 106 ላይ ተሻሽሎ ማየት የሚፈልጉትን ነገር
በዚህ የመወያያ ጊዜ Metro ከዋና ዋና የማኅበረሰብ ድምፆችን ለማዳመጥ በአውቶቡስ ፌርማታዎች ከተገልጋዮች ጋር፣ ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር፣ እንዲሁም ከማኅበረሰብ ተኮር ተቋማት ጋር ይወያያል።
Metro በዚህ ጥናት ውስጥ ማኅበረሰቡን ማካተትና ውሳኔዎቹ የማኅበረሰቡን ፍላጎትና እይታ መሠረት ያደረገ እንዲሆን ቆራጥ አቋም አለው።
ከእርስዎ ልንሰማ እንወድዳለን
የሚከተሉትን መንገዶች በመጠቀም ሐሳብዎን ሊያደርሱን ይችላሉ፦
መጠይቁን ከኦክቶበር 3፣ 2025 በፊት ሞልተው ይላኩልን።
በቅርቡ በምናደርጋቸው የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይቶች ላይ ይገኙና ሐሳቦችዎን ለቡድናችን አባላት ያካፍሉ።
- ● Renton Library – Resource Fair: ሐሙስ፣ ሴፕቴምበር 18፣ 2025፣ 1፡00 እስከ 3፡00 pm.
- Skyway Library – Drop-in Tech Help: ሠኞ፣ ሴፕቴምበር 22፣ 2025፣ 12፡30 እስከ 3፡00pm
ወደ 10 % ዲዛይን መድረስ
በአሁኑ ጊዜ ፕሮጀክቱ በዕቅድ ደረጃ ላይ ይገኛል። በዚህ ደረጃ፣ የጥናት ቡድኑ አካባቢያዊ ድርጅቶችን፣ የማኅበረሰብ አባላትን እና ሌሎች ዐበይት ቡድኖችን ያወያያል። ይህም የማሻሻያ ሐሳቦችን በቅደም ተከተል እንድንለይ ይረዳናል። ዕቅዱን ወደ ማጠቃለልና ወደ ግንባታው ሂደት ስንገባም ማኅበረሰቡን ማወያየታችንን እንቀጥላለን።
ያግኙን፤
ስለ ፕሮጀክቱ ጥያቄ ወይም ሐሳብ ካለዎት community.relations@kingcounty.gov ላይ ኢሜይል ያድርጉልን። ወይም በስልክ ቁጥር 206-263-9768 ላይ ይደውሉልን።
