የኪንግ ካውንቲ Metro ለስደተኛ ደንበኞቻችን ያለው ኃላፊነት
ይህ የብሎግ ልጥፍ በእነዚ ቋንቋዎች ይገኛል፡
በኪንግ ካውንቲ Metro ላይ፣ የግል መረጃ አያያዛችን እና ከዩኤስ ኢሚግሬሽንና ጉምሩክ ማስፈጸሚያ (Immigration and Customs Enforcement፣ ICE) እና ከትራንስፖርት ደህንነት አስተዳደር (Transportation Security Administration፣ TSA) ጋር ከስደተኞች ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ መተባበራችንን በተመለከተ አንድ አንድ ጥያቄዎች አልፎ አልፎ ይደርሰናል።
Metro፣ ORCA፣ Sound Transit እና ሌሎች የORCA ትራንዚት ኤጀንሲዎች የደንበኞችን ግላዊ መረጃ ለICE ወይም ለTSA አያካፍሉም። ይህ የግላዊ መረጃ የORCA ካርዶችን፣ ሌሎች የመጓጓዣ ትኬቶችን ወይም የመጓጓዣ ታሪፎችን ለማግኘት ወይም ለማዘመን ብለው ለትኬት ተቆጣጣሪ፣ ለህዝብ መጓጓዣ የደንበኞች አገልግሎት አባል፣ የመጓጓዣ አገልግሎት ፖሊስ፣ የመጓጓዣ አገልግሎት ደኅንነት ባለሥልጣን፣ ወይም ለሌላ የመጓጓዣ አገልግሎት ኮንትራክተሮች፣ ሠራተኛ ወይም ድህረ ገጽ ላይ ያጋሩትን መረጃዎችን እና ሎሎችን እዚህ ላይ ያልተጠቀሱ መረጃዎችን ያጠቃልላል።
በተጨማሪም፣ በስቴት ህግ፣ በፌደራል ህግ ወይም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካልሆነ በስተቀር፣ የኪንግ ካውንቲ ኮድ 2.15.010 እንዲህ ይላል:
- “ማንኛውም ግለሰብ በዜግነቱ ወይም በስደት ሁኔታው ምክንያት የካውንቲ አገልግሎትን ሊከለከል አይችልም።”
- “የኪንግ ካውንቲ ሰራተኞች፣ ወኪሎች ወይም ኤጀንሲዎች ስለዜግነት፣ የኢሚግሬሽን ሁኔታ ወይም ስለማንኛውም ሰው የትውልድ ሀገር መረጃ ከህዝብ አባል መጠየቅ ወይም መጠየቅ አይችሉም።”
- “ሁሉም የኪንግ ካውንቲ ወኪሎች ሰዎችን ወደ ICE እደውላለሁ በማለት ማስፈራራት ወይም ከስደት ጋር የተያያዘ ሌላ እርምጃ እወስዳለው በማለት ሰዎችን በቃላት መሳደብ አይችሉም።”
- “የኪንግ ካውንቲ ወኪሎች አገልግሎቶችን ለመስጠት አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር የግል መረጃን መያዝ ወይም ማጋራት አይችሉም። ነገር ግን አገልግሎት በመስጠት ሂደት ላይ ስለ ዜግነት ወይም የስደት ሁኔታ መረጃን ለሌሎች ኤጀንሲዎች እንዲልኩ ተፈቅዶላቸዋል።”
- “የኪንግ ካውንቲ ወኪሎች የፌደራል የኢሚግሬሽን ህግን ሲቪላዊ ማስፈጸሚያ ለማመቻቸት ጊዜን፣ ገንዘብን ወይም ሌሎች ሀብቶችን ማውጣት አይችሉም። ሆኖም፣ የካውንቲ ሰራተኛ የአንድ ሰው ዜግነትን ወይም የኢሚግሬሽን ሁኔታን ለፌደራል ኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ለመላክ ወይም ከነሱ ለመቀበል አይታገድም።”
ከላይ እንደተገለፀው የመጓጓዣ አገልግሎት ፖሊስ፣ የመጓጓዣ አገልግሎት ደኅንነት ባለሥልጣን እና ሌሎች የመጓጓዣ አገልግሎትሰራተኞች እና ኮንትራክተሮች ስለ አንድ ሰው ዜግነት፣ የኢሚግሬሽን ሁኔታ ወይም የትውልድ ሀገር መረጃ አይጠይቁም። የመጓጓዣ አገልግሎት ፖሊሶችን እና የመጓጓዣ አገልግሎት ደህንነት ባለስልጣናትን በቀላሉ እንዲለዩ ለማገዝ፣ እባክዎን የህግ ማስከበር ቁጥጥር ፅ/ቤት “በኪንግ ካውንቲ Metro የመጓጓዣ አገልግሎት እና የሳውንድ የመጓጓዣ አገልግሎት ባቡር ላይ የህግ አስከባሪ የማህበረሰብ መመሪያን” (በእንግሊዘኛ) ይመልከቱ።
እባክዎ ያስተውሉ፣ ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች ቢኖሩም፣ የአሽከርክሪዎቻችንን ህግና ደንብ እስካከበሩ ድረስ የ ICE እና TSA ባለስልጣናት በትራንዚት ላይ መጓዝ ይችላሉ። የሰሜን ምዕራብ የስደተኞች መብቶች ፕሮጀክት (Northwest Immigrant Rights Project) “መብቶችዎን ይወቁ” የሚሉ መርጃዎችን በብዙ ቋንቋዎች ያቀርባል። የአንድ ሰው ዜግነት ምንም ይሁን ምን እነዚህ መብቶች ለሁሉም ግለሰብ ተግባራዊ ናቸው።
